Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ota

Office of the Tenant Advocate
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about Office of the Tenant Advocate services for Amharic speakers.

የኤጀንሲ ስም:    የተከራይ ተሟጋች ቢሮ (Office of the Tenant Advocate)

ራእይ:

የተከራይ ተሟጋች ቢሮ (Office of the Tenant Advocate (OTA)) ራእይ ተከራዮች ከአከራይዎች ጋር በሚኖራቸው ክርክሮች የቴክኒካል ምክር እና ሌሎች የህግ አገልግሎቶችን መስጠት፤ ተከራይ ማህበረሰቡን ስለተከራይ መብቶች እና የኪራይ ቤቶችን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች ማስተማርና መረጃን መስጠት፤ በህግ አወጣጥ፣ ደንብ ድንጋጌ እና በፍርድ-ቤት ዘርፎች ለዲስትሪክቱ ተከራዮች መብቶች እና ፍላጎቶች መሟገት፤ እና ለተፈናቀሉ ተከራዮች የተወሰነ የአስቸኻይ መኖሪያ ቦታ እና ለተከራይ ቦታ የመቀየሪያ ወጪዎች የሚሆን የገንዘብ እርዳታ ማቅረብ ነው።

ዋና ዋና ፕሮግራሞች:  

የአስቸኳይ መኖሪያ ቦታ (Emergency Housing)

ኦቲኤ(OTA) በእሳት፣ ጎርፍ፣ ወይም መንግስት መዘጋት ምክንያት ለሚፈናቀሉ ተከራዮች የተወሰነ የአስቸኳይ ግዜ መኖሪያ ቦታ እና ቦታ ለመቀየሪያ ወጪ የሚሆን የገንዘብ እርዳታን በሚከተሉት አገልግሎቶች በኩል ያቀርባል

ኦቲኤ የትምህርት ተቋም (OTA Educational Institute)

ኦቲኤ (OTA) ለተከራዮች ስለመብታቸው እና ከኪራይ ቤቶች ጋር ስለየተያያዙ ሌሎች አሳሳቢ ጉዳዮች መረጃ ለማስጨበጥ በተለያዩ ዘርፎች ትምህርታዊ ሴሚናሮችን ያካሂዳል።

 

ኦቲኤ የመኖሪያ ቦታ እርዳታ እና የማህበረሰብ አገልግሎት (OTA Housing Assistance and Community Service)

ኦቲኤ(OTA) ተከራዮች ካከራዮች ጋር ያላቸውን ክርክሮችን ስለመፍታት ያማክራል፤ የህግ ጭብጥ-ነገሮችን እና የተከራዮችን እና የአከራዮችን መብቶችን እና ሀላፊነቶችን ለይቶ ያወጣል፤ እናም የከሳሽ አቤቱታን ማስገባትን የመሳሰሉ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል የህግ እና የቴክኒካል እርዳታን ይሰጣል።  

ኦቲኤ የህግ ውክልና (OTA Legal Representation)

አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ኦቲኤ(OTA) በራሱ ተቀጣሪዎች በኩል ለተከራዮች ተወክለው የሚቆሙ ተወካዮችን ያቀርባል ፤ እንዲሁም፣ ሌሎቹን ጉዳዮችን የነጻ የህግ አገልግሎት ወደ ሚሰጡ ወይም ወደ ተኮናተረው የህግ አገልግሎት ሰጭዎችና ጠበቆች ጋር በምሪት ይልካል።

 

የኦቲኤ የፖሊሲ ሙግት (OTA Policy Advocacy)

ኦቲኤ(OTA) በዲስትሪክቱ ውስጥ በተሻለ መልኩ ተከራይን የሚከላከሉ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ለማበረታታት፣ የዲሲ ካውስል (DC Council)፣ የከንቲባ ቢሮ (Mayor’s office)፣ ስራ-አስፈጻሚ ኤጀንሲዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ባለጋራ ተከራዮች፣ ተሟጋቾች እና ሌሎችንም ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ - ካልሆኑ መኮንኖች እና ተቋማት ጋር ይሰራል።

አገልግሎቶች

ኦቲኤ(OTA) ለተከራይ ማህበረሰቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ ተከራዮችን ካከራዮች ጋር ስለሚኖሩ ክርክሮችን ስለመፍታት ያማክራል፤ መብቶቻቸውን እና ሀላፊነቶቻቸውን የሚመለከቱትን የህግ ጭብጥ-ነገሮችን ለይቶ ያወጣል፤ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ በራሱ ተቀጣሪዎች በኩል ለተከራዮች ተወክለው የሚቆሙ ተወካዮችን ያቀርባል፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ በተሻለ መልኩ ተከራይን የሚከላከሉ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ለማበረታታት ከዲሲ ካውስል (DC Council) ፣ የከንቲባ ቢሮ (Mayor’s office) ፣ ፍርድ ቤቶች ፣ ባለጋራ ተከራዮች ፣ ተሟጋቾች እና ሌሎችንም  ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ -ካልሆኑ መኮንኖች እና ተቋማት ጋር ይሰራል። ኦቲኤ (OTA) በተለያዩ ዘርፎች ትምህርታዊ ሴሚናሮችን ያካሂዳል። ለተወሰኑ አስቸኳይ መኖሪያ ቦታዎች የገንዘብ እርዳታ ይሰጣል። 

 

የትርጉም አገልግሎቶች

ስለ የተከራይ ተሟጋች ቢሮ (Office of the Tenant Advocate) ጥያቄዎች ካሎት፣ ቢሯችንን በ (202) 719-6560 ማግኘት ይችላሉ። ቢሯችን ሲደውሉ ወይንም ሲመጡ እርዳታ ልንሰጦ እንድንችል፣ የሰራተኛችን አባል እርሶን በወቅቱ ከሚገኝ አስተርጓሚ ጋር ማገናኘት መቻላቸውን ያረጋግጣሉ።

የምንገኝበት አድራሻ: 

የተከራይ ተሟጋች ቢሮ(Office of the Tenant Advocate)

ሪቭስ ማእከል(Reeves Center)

2000 14th Street, NW Suite 300-N

Washington, DC 20009

ስልክ: (202) 719-6560

ፋክስ: (202) 719-6586

www.ota.dc.gov

የስራ ሰዐታት:ከሰኞ  አስከ አርብ፣ 8:45 AM to 4:45 pm